በICT ዲፓርትመን ለትብብር ስልጠና እና ለስራ ትስስር አገልግሎት የሚውሉ MPTC job portal Apparentship management system የተሰኙ ሶፍት ዌሮችን ማበልጸጉን አሳወቀ፡፡
ሶፍት ዌሮቹ ሰልጣኞቹን ከቀጣሪ እና ለትብብር ስልጠና አገልግት ከሚሰጡ ድርቶ ጋር በኦንላይን ማገናኘት የሚያስችሉ እንደሆኑ የICT ዲፓርትመንት ተጠሪ አቶ ተመስን እንዳክመው ገልጸዋል፡፡
ሶፍት ዌሮችን ለማበልጸግ ሰልጣኞች ለትብብር ስልጠና ለመውጣት የሚያጋጥማቸውን ችግር መነሻ እንደሆናቸው እና አሰልጣኝ ምንዳዬ፣ ያሬድ እና በጋራ በመሆን መስራታቸውን ገልጸዋል፡፡
Apparentship management system ድርጅቶቹ አገልግሎት የሚሰጡባቸውን ዘርፎች በተመለከተ ሙሉ መረጃ እንደያዘ እና ሰልጣኞች በሰለጠኑበት ዘርፍ ለትብብር ስልጠና በኦን ላይን ማመልከቻ ማቅረብ የሚያስችል እንደሆነ እና MPTC job portal ድርጅቶች ስራ የሚቀጥሩባቸውን ዘርፎች የያዘ በመሆኑ ሰልጣኞች ወደ የትኛው ድርጅት የስራ ቅጥር ደብዳቤ ማስገባት እንዳለባቸው እንደሚያሳውቅ የICT ዲፓርትመንት አሰልጣኝ አቶ ምንዳዬ ሲተሙን ለስራ ትስስር ክፍል ባሙያዎች ባስተዋወቁበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
የምክር እና ስራ ትስስር ክፍል ሀላፊ አቶ ሀይላይ ገ/መስቀል ሶፍት ዌሮቹ ሰልጣኞቹ ባሉበት ቦታ ሆነው ለትብብር ስልጠና ለስራ ትስስር መረጃ መስጠት እንደሚያስችሉ እና የወረቀት አልባ ስራን የሚያስቀሩ ናቸው ብለዋል፡፡
በሶፍት ዌሮቹ ለትብብር ስልጠና እና ለስራ ትስስር አገልግሎት ለመስጠት ሁለቱም ሶፍት ዌሮች ቢገናኙ እና ከስራ ክፍሉ የተሰጡ አስተያየቶች መስተካከል ያለበቸውን ጉዳዮች በትኩረት ታይተው ተስተካክለው ወደ ስራ ቢገባ ለሰልጣኞች የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ ይሆናል ብለዋል፡፡
.