Announcement ምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኮንሰርን ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሆን ያሰለጠናቸውን 38 ሰልጣኞች አስመረቀ፡፡

ምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኮንሰርን ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሆን ያሰለጠናቸውን 38 ሰልጣኞች አስመረቀ፡፡

03rd September, 2025

ምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኮንሰርን ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሆን ያሰለጠናቸውን 38 ሰልጣኞች አስመረቀ፡፡

ነሐሴ 16/2017ዓ.ም 

ምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኮንሰርን ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሆን ያሰለጠናቸውን 38 ሰልጣኞች አስመረቀ፡፡

ኮሌጁ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ዜጎችን ለተሻለ ህይወት ለማብቃት በአጫጭር መርሀ ግብር ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ስራ ዓለም እንዲሰማሩ ይሰራል፡፡ በዚህም ኮሌጁ ከኮንሰርን ኢትዮጵያ ጋር በመሆን በምግብ ዝግጅት፣ በጨርቃጨርቅ እና በጸጉር ስራ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 38 ሰልጣኞች አስመረቀ፡፡

በእለቱ ለተመራቂ ሰልጣኞች የስራ መመሪያ የሰጡት የኮሌጁ የሰልጣኝ እና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ጸጋዬ ሙጬ ሰልጣኞች በኮሌጁ ያገኙትን ሙያ ይዘው በስራ አለም በመቀላቀል የራሳቸውን እና የሀገራቸውን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳባቸው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ 

በምርቃቱ የተገኙት የኮሌጁ የሬጅስትራር ክፍል ሀላፊ አቶ ሚካኤል ካሳሁን ለሰልጣኞች እንኳን ደስ አላችሁ መልእክት በማስተላለፍ ለተመራቂ ሰልጣኞች ሰርፍኬት ሰተዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with