Announcement በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢንርፕራይዞች ርክክብ

በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢንርፕራይዞች ርክክብ

15th January, 2026

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር የስራ ሂደት በየካ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ድጋፍና ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ 9 በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢንርፕራይዞች ርክክብ አደረገ፡፡

በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ተደራጅተው እየሰሩ ያሉ በየካ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ድጋፍና ክትትል  ሲደረግላቸው የነበሩ 9 ኢንርፕራይዞች በምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ርክክብ ተካሂዷል፡፡ርክክብ የተካሄደው ኮሌጆች በአካባቢ ጸጋ ተለይተው በተሰጡ የሙያ ዘርፎች መሰረት ድጋፍ እና ክትትል እንዲያደርጉ ለማድረግ ታስቦ መካሄዱን የምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኮሌጁ የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን አቶ ብርሀኑ ቶሎሳ ገልፀዋል፡፡

በርክክቡ የምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን፣ የየካ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን፣የምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኮተቤ ካምፓስ ም/ዲን እና አስተባባሪ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ርክክቡ በሰነድ እና ቦታው ድረስ በአካል በመሄድ ተካሂዷል።

በቀጣይ ለኢንተርፕራይዞች  አሰልጣኞችን በመመደብ ፍላጎትን መሰረት  ያደረገ በአራቱም የድጋፍ ማዕቀፎች ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ የኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንደሚሰራ አቶ ብርሀኑ ገልፀዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with