Announcement የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ እና ርክክብ ተካሄደ።

የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ እና ርክክብ ተካሄደ።

20th August, 2025

ምሥራቅ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት አመት እቅድ ምክትል ዲኖች፣ ዳይሬክቶሬቶች፣ ዲባርትመንት ሀላፊዎች እና የስራ ክፍል አስተባባሪዎች በተገኙበት እቅድ ትውውቅ እና ርክክብ ተካሄዷል።

ኮሌጁ በ2018 በጀት ዓመት የተቋም ግንባታና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ከማሳደግ አንጻር በተቋም የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት 100% እንዲሰጡ ለማድረግ ትኩረት ተደርጎ ይሰራል።

በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋሉ ሌብነትና የብልሹ አሰራር ማክሰሚያ ስርዓት 100% በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግ።

ብዙሃን መገናኛ አውታሮችን በመጠቀም የአገልግሎት ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚዲያ ሽፋን በመስጠት የተገልጋይና የአገልጋይ መድረክ በመፍጠር በቋሚነት እንዲሳተፉ ማድረግ።

48 ንዑስ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡ 

ከአቅርቦት መር ወደ ፍላጎት መር  የስልጠና ሥርዓት በማጠናከር የስልጠና አግባብነትና ጥራትን ማሻሻል፤ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና በመደበኛ አሁን ካለበት 38% ወደ  81% ማድረስ እና በአጫጭር ጊዜ ስልጠና አሁን ካለበት 89.5% ወደ 90% በማስቀጠል የስልጠና  ጥራትን ለማሻሻል ይሰራል።

የ2017 ዓ.ም የመደበኛ መርሀ ግብር ሰልጠና አጠናቃቂዎች ውስጥ ከስራ ጋር የማስተሳሰር ምጣኔ አሁን ካለበት 76.4% ወደ 83% መድረሱን  በድህረ ስልጠና ጥናት ማረጋገጥ። 

ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎችና ተቋማት የመጡና የአቅም ግንባታ ስልጠና ለሚፈልጉ ለ160 ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት።

በበጀት ዓመቱን የስልጠና አጠናቃቂዎች ሰው ተኮር (ልል) ስልጠና 100% እንዲሰጥ በማድረግ ማብቃት።

ኮሌጁ አይሶ ISO 21001/2018 ሰርቲፋይድ እንዲሆን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

E- school net system የኦን ላይን  ሪጅስትሬሽን፣  የንብረት አያያዝና ብለንድድ ለርኒንግ (blended learning) የተግባራዊ በማድረግ ስልጠና አሰጣጡን ማዘመን።

በኮሌጁ ኢንተርፕራዝ በማቋቋም እና የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት  በራስ አቅም ገቢ የመሸፈን አቅማቸን አሁን ካለበት 13.5% ወደ 16% ማድረስ።

የነባር ኢንተርፕራይዞችን ድጋፍ በተመለከተ በ2017 በጀት ዓመት 544 ድጋፍ ያገኙ አዲስ ኢንተርፕራይዞችን ጨምሮ በ2018 በጀት ዓመት ወደ 979 ለማድረስ እንደሚሰራ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ዮሐንስ ሁንዱማ ገልጸዋል።

በተያያዘም የኮሌጁ የሰልጣኝ ልማት ም/ዲን አቶ ጸጋዬ ሙጬ የሰልጣኝ ልማት እቅድን ለዲፓርትመንት ሃላፊዎች በማስተዋወቅ የ2018ዓ.ም እቅድ ከዲፓርትመንት ተጠሪዎች ጋር ርክክብ አከካሂደዋል፡፡

በመጨረሻም የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ዮሐንስ ሁንዱማ ከምክትል ዲኖች የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ርክክብ አካሂደዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with