Announcement በምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ

በምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ

25th August, 2025

በምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ እና የቀጣይ የ2018 በጀት ዓመት በዝግጅት ምዕራፍ የሚሰሩ ስራዎች አቅጣጫ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

ኮሌጁ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ እና የቀጣይ የ2018በጀት ዓመት በዝግጅት ምእራፍ የሚሰሩ ስራዎች አቅጣጫ ላይ ከኮሌጁ ማኔጅንት እና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያይቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ አበይት ተግባራት 

ከአቅርቦት መር ወደ ፍላጎት መር የስልጠና ሥርዓት በማጠናር የስልጠና አግባብነትንና ጥራትን ከማስጠበቅ አኳያ 

•  የስራ ትስስር አፈጻጸም 76.4% 

•  የትብብር ስልጠና 97%፣  

•  የሰልጣኝ ምዘና 38% 

•  የአጫጭር ስልጠና ከ25ሺ በላይ ዜጎች ማሰልጠን መቻሉ

•  ዲጂታላይዜሽንን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ በኮሌጁ 2 ቴክሎጂዎችን በማማት ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉ

•  5 million Ethio coders ስልጠና በተመለከተ 2066 ተመዝግው 1666 መብቃታቸው

•  በአራቱ የድጋ ማእቀፍ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 1155 ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ለማድረግ ታቅዶ 1202 ድጋፍ መደረጉን፣ 

•  ከእሴት ሰንሰለት ትንተና 1 ለማድረግ ታቅዶ 1 በመከናወኑ አፈጻጸሙ 100% 

•  15 ቴክኖሎጂዎችን ለመስራት ታቅዶ 14 መሰራቱን፣

•  በቴክኖሎጂ ሽግግር 0.575/0.93 በአጠቃላይ 62% ማከናወኑን

•  1 ጥናትና ምርምር መሰራቱን 

•  በፋሽንሾ 12 ኢንስፓሬሽን መሰራቱ 

•  በአጠቃላይ በሀገር ደረጃ 5 ሜዳሊያ በአተማ ደረጃ 14 ሜዳያ ማግኘት መቻሉ 

•  በውስጥ አቅም ከተጠገኑ ማሽኖች የዳነ ሀብት525058 መሆኑ

•  የኢንደስትሪ አሰልጣኝ መፍራ መቻሉ

•  የሴቶች ተሳትፎ 29% ለማድረስ ታቅዶ 31.7% ማድረስ መቻሉን 

•  በፕሮጀክት ቤዝድ የሰለጠኑ አሰልጣኞችን በተለያዩ ሙያዎች 140 ማሰልጠን መቻሉ 

•  መመዘን ከነበረባቸው 421 አሰልጣኞች 281 ለምዘና የተላኩ ሲሆን 133 መብቃታቸውን ተገልጿል፡፡

በቀጣይ በ90 ቀናት እቅድ 

•  የአሰልጣኞች እና የሰልጣኞች ምዘና 

•  የተመራቂ ሰልጣኞች ከስራ ጋር ማስተሳሰር 

•  የተሰሩ ቴክሎጂዎች ሙሉ በሙሉ ማሸጋገር 

•  ምሥራቅ ኮቬት በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ መግባት የሚጀምርበት

•  የISO 21001፡2018ና በካይዘን ስራዎች ጨርሶ በማጠናቀቅ

•  የE- School ተግባራዊ ማድረግ 

•  የአረንጓዴ አሻራ ተግባራዊ ለማድረግ 3ሺ ችግኞች ተከላ ማካሄድ እና የተተከሉትን መንከባከብ

•  ለ20ሺ የስራ እድል ለሚፈጠርላቸው ዜጎች ስልጠና መስጠት

•  Ethiocoders ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኛ እና ሰልጣኝ መውሰድ እንዳለበት

•  ፋይዳ መታወቂያ ያላወጡ የኮሌጁ ሰራተኞች ማውጣት እንዳባቸው 

•  ኢንተርፕራይዞች በLMIS እንዲመዘገቡ 

•  የክረምት የበጎ አድራጎት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with