Announcement በቴክስታይል ጋርመንት ዲፓርትመንት በቀጣይ 2 ሳምንት ውስጥ የአሰልጣኞች የመብቃት ምጣኔ100% ለማድረስ እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

በቴክስታይል ጋርመንት ዲፓርትመንት በቀጣይ 2 ሳምንት ውስጥ የአሰልጣኞች የመብቃት ምጣኔ100% ለማድረስ እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

20th August, 2025

በቴክስታይል ጋርመንት ዲፓርትመንት በቀጣይ 2 ሳምንት ውስጥ የአሰልጣኞች የመብቃት ምጣኔ100% ለማድረስ እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

በምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቴክስታይል ጋርመንት ዲፓርትመንት ከተመዘኑት 20 አሰልጣኞች ውስጥ 20ዎቹም መብቃታቸውን ዲፓርትመንት ተጠሪው አቶ ደራራ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም 11 አሰልጣኞች ምዘና ለመውሰድ መመዝገባቸውን እና በ2 ሳንት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የአሰልጣኝ የመብዋት ምጣኔ 100% ለማድረስ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ዲፓርትመንቱ የአሰልጣኞች የመብቃት ምጣኔ ከፍተኛ እንዲሆን እንደ ዲፓርትመንት የተጠቀምነው እስትራቴጂ በመጀመሪያ ምዘና ላይ የነበሩ ክፍተቶችን ለይቶን በማውጣት የተለዩ ክፍተቶች ላይ ሁሉም አሰልጣኝ እርስ በእርስ በመደጋገፍ ለ10 ቀናት ሙሉ ቀን ስልጠና እንዲወስዱ እንደተደረገ ዲፓርትመንት ተጠሪው ገልጸዋል፡፡

በመቀጠልም በዲፓርትመንቱ ሞዴል ምዘና በማዘጋጀት አሰልጣኞቹን መዝነን ብቁ መሆናቸውን የማረጋገጥ እና ያልበቁትን በድጋሚ ክፍተቶቻቸው በመለየት እራሳቸውን እንዲያበቁ ካደረግን ቦሃላ ድጋሚ ሞዴል ምዘና መዝነን አብቅተናል።

በተጨማሪም እንዱስትሪ ላይ በምን አይነት መልኩ እንደሚሰራ ዎሊሶ የሚገኝ እንዱስትሪ ለ5ቀን የኢንዱስትሪ ውስጥ ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡

በመጨረሻ 20 አሰልጣኞች አስመዝግበን ሁሉም የተመዘገቡት ተመዝነው 20ዎቹም አሰልጣኞች ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ማለፍ ችለዋል ብለዋል።

ቀሪዎቹ ያልተመዘኑ አሰልጣኞች ምዘና ለመውሰድ መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡

የኮሌጁ አመራሮች ላደረጉልን የሞራል ግንባታና ማበረታቻ እንዲሁም የግብዓት ድጋፍ እና ሌሎች እገዛዎችን ከፍተኛ ምስጋና በዲፓርትመንቱ ስም እናቀርባለን ብለዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with