Announcement የማእድ ማጋራት መርሀ ግብር

የማእድ ማጋራት መርሀ ግብር

15th January, 2026

የማእድ ማጋራት መርሀ ግብር ተካሄደ።

በምሥራቅ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018ዓ.ም የገናን በአል ምክንያት በማድረግ ለኮሌጁ ሰራተኞች እና በኮሌጁ ድጋፍ ለሚያድጉ ልጆች ማእድ  አጋርቷል።

ኮሌጁ ከሚያከናውናቸው ሰው ተኮር ተግባራት መካከል አንዱ በበአላት ጊዜ የማእድ ማጋራት ነው። ማእድ ማጋራት መደጋገፍን፣ አንድነትንና መተሳሰብን የሚያጎላ መልካም እሴት ነው ይህ እሴትም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ዮሐንስ ሁንዱማ ተናግረዋል።

ድጋፉ የኮሌጁ ሰራተኞች እና ድጋፍ የሚደረግላቸው ልጆች በዓልን በደስታ እንዲያሳልፉ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

ይህ ሰው ተኮር ተግባር ኮሌጁ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የማእድ ማጋራት ሥነ- ሥርዓቱ የተገኙት የኮሌጁ የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን አቶ ብርሀኑ ቶሎሳ የማእድ ማጋራት መርሀ ግብሩ አብሮነትን ለማሳየት የሚካሄድ ነው ብለዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with