Announcement የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ  አፈፃፀም ደንብ  ዙሪያ ለምደባ እና ቅሬታ ኮሚቴ አባላት  ስልጠና ተሰጠ።

የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ  አፈፃፀም ደንብ  ዙሪያ ለምደባ እና ቅሬታ ኮሚቴ አባላት  ስልጠና ተሰጠ።

04th September, 2025

የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ  አፈፃፀም ደንብ  ዙሪያ ለምደባ እና ቅሬታ ኮሚቴ አባላት  ስልጠና ተሰጠ።

ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ  የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ በተጠሪ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለሚካሄደው ዞኒንግና ዲፈረንሼሽን ስትራቴጂ ትግበራ   የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ  አፈፃፀም ደንብ  ዙሪያ ለምደባ እና ቅሬታ ኮሚቴ አባላት  ስልጠና ተሰጥቷል።

በቢሮ ሀላፊ ደረጃ  የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ  የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ  በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የስትራቴጂው መተግበር  በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሰልጣኝ አሰልጣኝ እንዲሁም የማሰልጠኛ ክፍሎች ጥምርታን በማጣጣም ኮሌጆች አካባቢያዊ የመልማት ፀጋቸውን መሰረት አድርገው ጥራት ያለው ስልጠና ለመስጠት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የኮሚቴው አባላት በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት በታማኝነት አሰልጣኞችን በማወዳደር የምደባ ስራ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

በስልጠናው የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ  አፈፃፀም ደንብ ዙሪያ በአዲስ አበባ ፐብሊክ የሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ገለፃና ማብራሪያ ተደርጓል።

በስልጠናው ለቢሮው ተጠሪ የሆኑ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት እንዲሁም የምደባ እና የቅሬታ ኮሚቴ አባላት  ተገኝተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with