Announcement በምሥራቅ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአመራሮች የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር ተካሄደ።

በምሥራቅ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአመራሮች የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር ተካሄደ።

20th August, 2025

በምሥራቅ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአመራሮች የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር ተካሄደ።

በመርሀ ግብሩ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ዮሐንስ ሁንዱማ፣ ም/ዲኖች፣ ዳይሬክቶሬቶች፣ ዲፓርትመንት ተጠሪዎች እና የስራ ክፍል አስተባባሪዎች የተሳተፉበት የእውቀት ሽግግር ተካሂዷል።

በእለቱም የቢዝነስ ዲፓርትመንት አሰልጣኝ እና የኮቬት ስራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ በየነ የማንነት ተክለ ስብእና ከ4 አእዋፍ ጠባይ አንጻር በሚል ርእስ ያዘጋጁትን ሰነድ መነሻ አድርገው ለአመራሩ ያላቸውን እውቀት አካፍለዋል።

በቡድን ሥራ እንዴት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል እና የተለያዩ ባህርያት ካላቸው መሪዎች ጋር እንዴት አብሮ መስራት እንደሚቻል ከ4ቱ አእዋፍ ጠባይ አንጻር በማነጻጸር አብራርተዋል።


የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ዮሐንስ ሁንዱማ የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር እንደ ኮሌጅ ዘግይቶ ቢጀመርም በቀጣይ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች የእውቀት ሽግግሩ እንደሚቀጥል እና መሰል ውይይቶች በኮሌጁ ባሉ የተለያዩ የስራ ክፍሎች መካሄድ እንዳለበት ገልጸዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with