Misrak Polytechnic College

ምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ47 የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 2236 ሰልጣኞች አስመረቀ።

13 Sep 2023

ኮሌጁ በሶስት ካምፓሶች እና በሁለት ክላስተር ኮሌጆች ከደረጃ 1 - 5 ያሰለጠናቸውን 2236 ሰልጣኞች በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ቴክኒክ ፣ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር ካሉ 14 ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር አስመረቀ።

በምርቃቱም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ክብርት ሙፈርያት ካሚል፣የአዲስ አበባ ብልፅግና ፖርቲ ሃላፊ መለስ አለሙ፣የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩር ሻሌ፣የኮሌጅ ዲኖች እና አሰልጣኞች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ አስመርቋል።

ሰልጣኞች በሰለጠኑበት ሙያ ሀገራቸውን በማገልገል በተለይ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርት በመተካት በኢኮኖሚው ረገድ ከፍተኛ ስራ ይጠበቅባችኋል በማለት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተመራቂዎች መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።